የአዋጭ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃላ/የተ/መሠ/የኅብረት ሥራ ማኅበር አባላት እና ሠራተኞች የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብርን ምክንያት በማድረግ ችግኝ ተከሉ፡፡ (ሐምሌ 22 ቀን 2011 ዓ.ም አዲስ አበባ)

አዋጭ የገ/ቁ/ብ/ኃላ/የተ/መሰ/ የኅብረት ሥራ ማኅበር ሀገራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በማሰብ የኅብረት ሥራ ማኅበሩን አባላት እና ሠራተኞች በማስተባበር ሐምሌ 22 ቀን 2011 ዓ.ም አረንጓዴ አሻራ በሚል መሪ ቃል በተደረገው ሃገራዊ ንቅናቄ ተሳታፊ በመሆን በአቃቂ ቃሊቲ የአረጋዊያን መርጃ መርጃ ማዕከል ቅጥር ግቢ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር አካሂዷል፡፡