የአዋጭ መስራች አባላት

አባላቱንና ካፒታሉን ማሳደግ የማህበሩ የስኬት መጀመሪያ መሆኑን የሚያምነው አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/ህ/ስራ ማህበር በ2010ዓ.ም. የአባላቱን ቁጥር 11,241 በማድረስ የማህበሩን ጠቅላላ ሀብት ደግሞ ወደ 216,886,116.41(ሁለት መቶ አስራስድስት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሰማንያ ስድስት ሺ አንድ መቶ አስራስድስት ከአርባ አንድ ሳንቲም) አድርሷል፡፡

እነዚህን ተከታታይ ስኬቶችን በማየት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማህበራት ማደራጃ ዘርፍ እና ከአራዳ ክፍለ ከተማ ማህበራት ማደራጃ የስራ ሂደት ማህበራችን በከተማችንና በክፍለ ከተማችን ካሉ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበራት ጋር ተወዳድሮ አንደኛ በመውጣት የሁለት ዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል፡፡ በፌዴራል ህብረት ስራ ኤጀንሲም የተለያዩ ሽልማቶችን ያገኘ ሲሆን ከፍተኛ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬትም ተሰጥቶታል፡፡