አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ሀላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማህበር ለታላቁ የኢትዮጲያ ህዳሴ ግድባ ግንባታ ተጨማሪ የ500,000 /አምስት መቶ ሺህ/ ብር ቦንድ ገዛ

የታላቁ የኢትዮጲያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እንዲጠናቀቅ ከህፃን እስከ አዋቂ ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንዳለበት የአራዳ ክ/ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ የግድቡን ግንባታ ዳር ለማድረስ ቦንድ በመግዛት ሀገራዊ ግዴታችንን እንወጣ በሚል ሀሳብ የ500,000 /አምስት መቶ ሺህ/ ብር ቦንድ በኅብረት ሥራ ማኅበሩ ስም ሲገዙ ያገኘናቸው በክፍለ ከተማው ወረዳ 7 የሚገኘው አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ሀላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማህበር መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዘሪሁን ሸለመ በየዓመቱ በኅብረት ሥራ ማህበሩ ስም ቦንድ በመግዛት በአጠቃላይ የአንድ ሚሊየን ሀምሳ ሺህ ብር ቦንድ ከመግዛታቸውም በላይ በግላቸው ደግሞ የአንድ ሺህ ብር ቦንድ መግዛታቸውን ጠቅሰው ኅብረት ሥራ ማህበሩ የታላቁ ህዳሴ ግድብ አልቆ ለህብረተሰቡ ጥቅም ላይ እስኪውል የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡