Error message

Deprecated function: The each() function is deprecated. This message will be suppressed on further calls in menu_set_active_trail() (line 2405 of /home/t40wi9z3tbcw/public_html/includes/menu.inc).

አዋጭ የዓለም የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት ቀንን ለ3ኛ ጊዜ በደማቅ ሁኔታ አከበረ!!

ጥቅምት 07 ቀን 2013 ዓ.ም. አዲስ አበባ (አዋጭ)

አዋጭ ዛሬ ጥቅምት 07 ቀን 2013 ዓ.ም. ”የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማኅበራት ለዓለም ማህበረሰብ ተስፋ ፈንጣቂዎች ናቸው፡፡“ (“Inspiring Hope for a Global Community”) በሚል መሪ ሀሳብ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ72ኛ በኢትዮጵያ ለ28ኛ ጊዜ የሚከበረውን የዓለም የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት ቀንን በካፒታል ሆቴል በደማቅ ሁኔታ አከበረ፡፡ በዚህም በዓል ላይ ክቡር ዶ/ር ኃይሌ ገብሬ የመጀመሪያው የህብረት ሥራ ኮሚሽን ኮሚሽነር፣ ክቡር አቶ ዑስማን ሱሩር የፌደራል ህብረት ሥራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር፣ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የፌደራል ህብረት ሥራ ኤጀንሲ ከፍተኛ አመራሮች፣ የህብረት ሥራ ማህበራት ባለቤቶችና አመራሮች፣ የህብረት ሥራ ማህበራት አቅም ገንቢ አካላትና ተወካዮች፣ ጋዜጠኞች፣ አርቲስቶች፣ የሚዲያ አካላት፣ የአዋጭ አባላት/አመራርና ሰራተኞች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው የህብረት ሥራ ቤተሰቦች ተገኝተዋል፡፡
የዚህ በዓል ዋና ዓላማ በሀገራችንና በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማህበራት የደረሱበትን የዕድገት ደረጃ፣ በዘርፉ የተገኙ ውጤቶችና ተሞክሮዎች የሚለዋወጡበት ስለ ዘርፉ አስፈላጊነት/ጠቀሜታ የዘርፉ ባለሙያዎች ትንታኔ የሚሰጡበት፣ ማህበራቱ ራሳቸው የእርስ በርስ ልምድ የሚቀያየሩበት፣ የዘርፉን ፋይዳና ስኬቶች አስመልክቶ የበለጠ አጠናክሮ ለማስቀጠልና የዘርፉን ማነቆዎች ለመፍታት የሚያስችሉ ጉዳዮች የሚዳሰሱበት መድረክ ነበር፡፡ በመሆኑም በዕለቱ ከታደሙት ህብረት ሥራ ማህበራት መካከል አዋጭን ጨምሮ ከአዳማ አብዲ ጉዲና የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ዩኒየን እና ከመቀሌ ፋና የወጣቶች የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማህበር ምርጥ ተሞክሮዋቸውን ለህብረት ሥራ ቤተሰቦች አካፍለዋል፡፡
በማስከተልም የዘርፉ መሰረታዊ ጉዳዮች ትኩረት እንዲያገኙ ለመመካከር ዕድል የሚሰጠውን ይህን መሰል በዓል በማዘጋጀት ረገድ እንደ አዋጭ ሁሉ ሌሎች አቻ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማህበራት ሀሳቡን በመጋራት በቀጣይ የባለቤትነት ድርሻውን እንዲጋሩ በሚለው ሀሳብ ዙሪያ በፌደራል ህብረት ሥራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዑስማን ሱሩር እና በሌሎች የሴክተሩ ባለሙያዎች ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡ በመጨረሻም አዋጭ በህብረት ሥራ ንቅናቄና በአዋጭ የስኬት ጉዞ ከፍተኛና አስተዋፅኦ ላበረከቱ የዘርፉ ባለሙያዎችና ሌሎች አካላት የምስጋና ሽልማት በመስጠት በዓሉ አክብሮ ውሏል፡፡