አዋጭ የአለም አቀፍ የገንዘብ እና ቁጠባ ቀንን አከበረ

World Council of Credit Union (ዓለም ዓቀፍ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማህበር ምክር ቤት) ከ1948 ዓ.ም. ጀምሮ በየዓመቱ የቁጠባና ብድር የህብረት ሥራ ቀን በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በጥቅምት ወር ሦስተኛው ሐሙስ በማክበር ላይ ይገኛል፡፡ ዘንድሮም በዓለም ለ70ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ27ኛ ጊዜ በድምቀት ይከበራል፡፡ የዚህ ዓመት መሪ ቃልም “Find your Platinum lining in Credit Union” በሚል እየተከበረ ይገኛል፡፡ አዋጭ የገ/ቁ/ብ/ኃ/የተ/የህ/ሥራ ማህበርም ይህንን ቀን በታላቅ ድምቀት በዛሬው ዕለት በግዮን ሆቴል በተለያዩ ዝግጅቶች በማክበር ላይ ይገኛል፡፡ በዝግጅቱም ላይ የተወካዩች ምክር ቤት ተወካይ ክቡር አቶ አሊ ኡስማን፣ የፌደራል ህብረት ሥራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ዑስማን ሱሩር፣ የሚዲያ ባለሙያዎች፣ ጋዜጠኞች እና ሌሎችም እንግዶች የተገኙ ሲሆን በተጨማሪም የህብረት ሥራ ማህበራት ለሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ እያበረከቱ ባሉት አስተዋፅዎ፣ የህብረት ሥራ ማህበራት ከየት ወዴት፣ ያሉባቸው ተግዳሮቶች እና የአዋጭ የገ/ቁ/ብ/ኃ/የተ/የህ/ስራ ማህበር ከምስረታ እስካሁን እንዲሁም የህብረት ሥራ ማህበር ስለሆነው ራቦ ባንክ ፅሁፎች ቀርበዋል፡፡